ሰለ ቤተ-ክርስትያን ዝም አልልም
ዐምደ ሃይማኖት የሚባለው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ምስጢር ላይ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተምር ርሱ ራሱ በግ ደሙም ወይን፤ ርሱ ሙሽራ ጐኑም የሕይወት ውሃ ምንጭ፤ ርሱ መምህር የአፉም ትንፋሽ የዕጣን መዐዛ፤ ርሱ መብራት መስቀሉም መቅረዝ፤ ርሱም የገነት ዛፍ የጸጋውም ወንጌል መዐዛው ያማረ አበባ፤ ርሱ የጽድቅ ፀሓይ ሐዋርያቱም የብርሃን ከዋክብት፤ ርሱ የበረከት ማዕድ ካህናቱም የምስጢር አገልጋዮች፤ ርሱ የቅድስና ልብስ ዲያቆናቱም በልብስነቱ ዘርፍ ኾነው ልብሰ ተክህኖውን የሚከብቡት የወርቅ ጸናጽል፤ ርሱ እረኛ ያመኑበትም የምስጢር በጎች፤ ርሱ ንጉሥ ሰማዕታቱም የመንግሥትን አዳራሽ የሚያስጌጧት ዕንቊዎች፤ ርሱ አውነተኛ የወይን ስፍራ መነኮሳቱም ለሚያዩት ሰዎች ለአይን ያማረ የጽድቃቸውም ፍሬ በሚያነብበው ሰው አፍ የሚጣፍጥ የወይን ዘለላዎች ናቸውና፡፡ አንባቢያን ሆይ ይህን የተናገረው በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ነው፡፡ ታድያ አሁን በአባቶቻችንና በእናቶቻችን አለፍ ካለም በአያቶቻችን እድሜ (ማለትም 20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን) የተነሱ ፕሮቲስታንቶች ሆኑ ተሐድሶዎች ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን ወንገልን አትሰብክም፣ ክርስቶስን ረስታዋለች፣ ክርስቶስን አትሰብክም ቢሉ ማን ያምናቸዋል፡፡ እኔ ግን ስለ ቤተ-ክርስትያኔ ዝም አልልም እናገራለሁ እጽፋለሁ!!! ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሚስጢር ባለቤት፤ የሞላች የሰፋች ይህ ቀረሽ የማትባል ስንዱ እመቤት፤ የሥልጣኔ መገኛ የኢትዮጵያ ባለውለታ እንደሆነች ለዘላለም እመሰክራለሁ!!! ዳግመኛም ድንግል መልአኩ...